• TN Green Trading
  • TN Green Trading
  • From Bean to Global Cup
  • Have any question? +251911759393
  • TN Green Trading
    TN Green Trading
    • Main Office
      Addis Ababa, Ethiopia
    • Trusted By
      200000 User
    • Email
      info@tngreentrading.com
    • Home
    • About us
      • Who We Are
      • Company History
      • Our Team
      • Testimonials
      • Faq
      • Gallery
    • Services
    • Events
    • Blog
    • Contact Us
  • Contact us
Home NEWS የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀ ሁኔታ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ!!

የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀ ሁኔታ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ!!

  • 10 Comments
  • tngreen
Dr Adugna
ይህ የተገለጸው ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልከውን ቡና በተመለከተ በባለፉት ሶስት ወራት በተከናወነው ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ክቡር የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ በውይይቱ ላይ ክቡር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ቁጥራቸው ከ140 የሚልቅ ላኪዎች እና ሌሎች የቡና ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ መንግስት ዘርፉን ለመደገፍ፣ ለማበረታታት እና ወደፊት ለመግፋት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመው ላኪዎችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በታማኝነት እና በትጋት በመስራት አ/አደሩ ተጠቃሚ የሚሆንበትን እና አገራችንም በዘርፉ የላቀ ደረጃ እንድትደርስ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ በልማቱ በኩል ዘመናዊ እና ቀልጣፋ የአመራረት ዘይቤ መከተል እንደሚገባ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትሩ በበጀት ኣመቱ በመንግስት የተቀመጠውን የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀ ሁኔታ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚጠበቅ እና ባሉ ችግሮችም ዙሪያ በግልጽ ተወያይቶ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተናግረዋል፡፡
ክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ዘንድሮ 600 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት እየሰራች መሆኗን የገለጹ ሲሆን በሩብ አመቱ 152 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጪ በመላክ 622.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 114 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 762.5 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት እንደተቻለ ተናግረዋል። ገቢው ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ47 በመቶ ዕድገት የተመዘገበበት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ክቡር አቶ ሻፊ ዑመር የባለስልጣን መ/ቤቱ ምክ/ዋና ዳ/ር እና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ የሶስት ወራት የቡና እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በኋላ የወጪ ንግድ መጠን የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ማግኘት እንዳለበት እንዲሁም በቡና የወጪ ንግድ የአመቱን ግብ በመጠን እና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳካት በቡና ዕሴት ሰንሰለት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በተቀናጀ አሰራር ለመፍታት መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
  • Tags: Businessconsultingfinance
  • Share:
Prev Article ከቻይና ዩናን ግዛት የመጣ ልዑክ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያየ
Next Article 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል

    Leave Your Comment Cancel Reply

    Your email address will not be published.*

    Recent Posts

    • 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል
    • የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀ ሁኔታ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ!!
    • ከቻይና ዩናን ግዛት የመጣ ልዑክ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያየ

    Recent Comments

    1. Johny on ከቻይና ዩናን ግዛት የመጣ ልዑክ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያየ
    2. Mike Pence on 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል
    3. Mike Pence on 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል

    Latest Posts

    • 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል
      3
      November 24, 2025
    • Dr Adugna
      የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀ ሁኔታ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ!!
      10
      November 24, 2025
    • ከቻይና ዩናን ግዛት የመጣ ልዑክ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ጋር
      ከቻይና ዩናን ግዛት የመጣ ልዑክ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያየ
      3
      November 3, 2025

    Tags

    Business consulting finance

    Contact Info

    Mon – Sat: 08:30 – 18:00

    +251911759393

    Addis Ababa, Ethiopia

    info@tngreentrading.com

    TN GREEN LOGO

    TN Green Trading is a reputable Ethiopian trading company that specializes in exporting high-quality coffee and importing essential industrial raw materials.

    Quick Links

    • Home
    • About
    • Services
    • Careers
    • Gallery
    • News
    • Contact Us
    • Event

    Blog List

    • 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል November 24, 2025
    • የበጀት ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀ ሁኔታ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ!! November 24, 2025

    Get In Touch

    If you Want to more information about us just enter your email

    • Copyrights © 2025 TN Green Trading. Designed by Ethio Technology

    Powered by
    ...
    ►
    Necessary cookies enable essential site features like secure log-ins and consent preference adjustments. They do not store personal data.
    None
    ►
    Functional cookies support features like content sharing on social media, collecting feedback, and enabling third-party tools.
    None
    ►
    Analytical cookies track visitor interactions, providing insights on metrics like visitor count, bounce rate, and traffic sources.
    None
    ►
    Advertisement cookies deliver personalized ads based on your previous visits and analyze the effectiveness of ad campaigns.
    None
    ►
    Unclassified cookies are cookies that we are in the process of classifying, together with the providers of individual cookies.
    None
    Powered by